ኢትዮጵያዊው ብርሃን
ኢትዮጵያዊው ብርሃን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን ሸዋ ቡልጋ ጽላልሽ ወይም ዞረሬ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰበካ ክልል ከአባታቸው ከካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ቅድስት እግዚእ ኃረያ መጋቢት ፳፬ ቀን ተፀንሰው፤ በ፲፩፻፺፯ ዓ.ም ታሕሣሥ ፳፬ ቀን ተወለዱ፡፡
በተወለዱ በሦስት ቀናቸው ከእናታቸው እቅፍ ወርደው «አሐዱ አብ ቅዱስ፣አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ» ብለው ሥላሴን አመስግነዋል፡፡ ወላጆቻቸውም ፍስሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ትርጓሜውም የጽዮን ተድላዋ ወይም ደስታዋ ማለት ነው፡፡ አባታቸው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲያስተምሯቸው አካባበቢያቸው ደግሞ በዘመኑ የነበሩ ልጆች ይማሩ የነበረውን ፈረስ መጋለብን፣ ቀስት መወርወርን፣ እርሻን እና አደንን አስተምረዋቸዋል፡፡
ስለ ሃገረ ስብከታችን
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ እንቅስቃሴ የጀመረችው ከስድሳ ዓመታት በፊት በ፲፱፻፴፯ ዓም እ.ኤ.አ. አካባቢ ነው። በዚያ ወቅት ወርልድ ፌዴሬሽን የተባለው እና ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ ድጋፍ ለማሰባሰብ በእነ መላኩ በያን አማካኝነት የተቋቋመ ድርጅት ቤተ ክርስቲያኒቱን ለምዕራቡ ዓለም ከማስተዋወቁም በላይ በአሜሪካ እንዴት መቋቋም እንዳለባት ያለውን እቅድ ለመንበረ ፓትሪያሪኩ ልኮ ነበር።
ይህንን መሠረት በማድረግ አባ ገብረ ኢየሱስ መሸሻ (በኃላ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ) እና አቶ አበራ ጀምበሬ እ.ኤ.አ. በ፲፱፻፶፪ ዓም ለቤተ ክርስቲያን መተከል የሚያስፈልጉትን ንዋያተ ቅድሳት በማምጣት ጥናቱን አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሱ። ከሁለት ዓመት በኃላም የሐረር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት የነበሩት ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ወደ አሜሪካ በመጡበት ጊዜ በአሜሪካ እና በካሪቢያን ደሴቶች ቤተ ክርስቲያንን ለመትከል ቅዱስ ሲኖዶስ ያሰበበት መሆኑን እና ይህም በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተለጡ። በተገባውም ቃል መሠረት እ.ኤ.አ. ጥቅምት ፳፭ ቀን ፲፱፻፭፱ ዓም ተመልሰው ወደ ሰሜን አሜሪካ በመምጣት ዛሬ የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና በመሆን የሚያገለግለውን የቅስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት አከበሩ።
ዓሣ አጥማጁ ስምዖን(ለሕፃናት)
በአዜብ ገብሩ
በአንድ ወቅት ምን ሆነ መሰላችሁ ጌታችን በባህር ዳር ቆሞ ሕዝብን ያስተምር ነበር ሕዝቡም ጌታችን የሚያስተምረውን ትምህርት በደንብ ይከታተሉት ነበር፡፡ ጌታችንም ድምጹ ለብዙ ሰዎች እንዲሰማ ወደ ስምዖን ታንኳ ላይ ወጣ፡፡ በታንኳይቱም ውስጥ ተቀምጦ ሕዝቡን አስተማራቸው፡፡
የእውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን መገለጫዎች
በቀሲስ ብርሃኑ ጎበና
ቤት የሚለው ቃል ወገን፤ ነገድ፤ ዘር፤ ትውልድ፤ ጉባኤ፤ ማኅበር ማለት እንደሆነ አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው ላይ ጠቅሰዋል፡፡(ኪ.ወ.ክ ገጽ 268) የያዕቆብ ወገን ቤተ ያዕቆብ (ቤተ እስራኤል)፤የዳዊት ወገን ቤተ ዳዊት እንዲባል በመንፈሳዊና በምሥጥራዊ ልደት ከክርስቶስ የተወለዱ ምእመናንም ቤተ ክርስቲያን ይባላሉ፤ ቤተ ክርስቶስ (የክርስቶስ ወገን) እንደ ማለት ነው፡፡ ዳሩ ግን በዘመናችን ስምና ግብር ለየቅል ሆነው በተቃራኒ ያሉት ወገኖች ሳይቀሩ ስሙን መጠሪያ አድርገው አናስተውላለን፤ ዘመናችን አማናዊቱ ቤተ ክርስቲያን ስምዋን ወስደው በሚጠሩ አስመሳዮች የተወረረችበት ወቅት በመሆኑ እውነተኛዋን ለይቶ ማወቅ ግድ ይላል፡፡