የምሥራቀ ፀሐይ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን

ለመንበረ ጵጵስናው የሚሆን ቤተ ክርስቲያን የማቋቋሙ ሥራ ብፁዕ አባታችን እና መሥራች ኮሚቴው ባደረጉት ጥረትም ግንቦት ፴ ቀን ፳፻፩ ዓም በዕለተ ጰራቅሊጦስ የምሥራቀ  ፀሐይ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ። አጥቢያው ባደረገው እንቅስቃሴ ከምሥረታው ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በርካታ ሥራዎችን ሰርቶ አሳይቷል፥ በዚህም በአርያነት ከሚጠቀሱት አጥቢያዎች አንዱ ሊሆን በቅቷል። የምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ከሚያከናውናቸው የዕለት ተዕለት ተግባራት ዋነኞቹ የሚከተሉት ይገኙበታል።

  • ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት የነግህ ፀሎት፣ ማታ የሰርክ ፀሎት
  • እሑድ የሥርዓተ ቅዳሴ፣ ከዚያም ሰንበት ት/ቤት ጉባኤ በየሰንበቱ
  • በየሳምንቱ ቅዳሜ ጠዋት ለወጣቶች ትምህርተ ሃይማኖት እንዲሁም ዝማሬ በእንግሊዝኛ
  • በየሳምንቱ ቅዳሜ ከሰዓት በኃላ ለሕፃናት የፊደል ቆጠራ፣ ዝማሬ እንዲሁም ትምህርተ ሃይማኖት ይሰጣል

እነዚህ አገልግሎቶች በየጊዜው ሳይስተጓጎል ይሰጣል፥ በተጨማሪ የሥርዓተ ተክሊል፣ የጥምቀት፣ እና የፍታት አገልግሎቶች በየጊዜው ይሰጣሉ።

Additional information