ቅዳሴ እና መጽሐፍ ቅዱስ
በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ
ቤተ ክርስቲያናችን ሥጋ ወደሙን የምታከብርበት የተለየ ሥርዓተ ጸሎት አላት፡፡ ይህ ልዩ የምስጋና ጸሎት ‹‹ጸሎተ ቅዳሴ›› ይባላል፡፡ ያለ ጸሎተ ቅዳሴ ሥጋ ወደሙ አይዘጋጀም (አይፈተትም)፡፡ ያለ ሥጋ ወደሙም ቅዳሴ አይቀደስም፡፡
በቤተ ክርስቲያን የታወቁና እስከአሁንም በአገልግሎት ላይ ያሉ ቅዳሴያት በዓይነት 14 ሲሆኑ ቀደም ባሉት ዘመናት በተለይ በወርኀ ጽጌ ይቀደስ የነበረ ‹‹መዓዛ ቅዳሴ›› የሚባል 15ኛ ቅዳሴም በቤተ ክርስቲያናችን ይገኛል፡፡
ጸሎተ ቅዳሴ መሠረቱ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ የዚህ አጭር ገጸ ንባብ /የመግቢያ ንግግር/ ዓይነተኛ ዓላማ ቅዳሴ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑን ግልጽ ማድረግ ነው፡፡
ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ተክለሃይማኖት ሕፃናት በወረብ አገልግሎት
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ሃገረ ስብከት የምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን የነገዋ የቤተክርስቲያን ተተኪ ሕፃናት በእለተ ሰንበት በወረብ አገልግሎት ላይ
ሕፃናቱን በጥበብ በሞገስ ያሳድግልን አሜን