ዛሬ የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው
ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተራራው ስብከቱ ፥ በአንቀጸ ብጹዓን ትምህርቱ፡- «ብፁዓን እለ ይላህዉ ይእዜ እስመ እሙንቱ ይትፌሥሑ፤ « ዛሬ የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው ፥ እነርሱ ደስ ይሰኛሉና፤ (መጽናናትን ያገኛሉና)፤» ብሏል። ቅዱሳን ሐዋርያትም በዚህ ላይ ተመስርተው፦ « እናንተ ኃጥአን እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት ዐሳብም ያላችሁ እናንተ ልባችሁን አጥሩ። እዘኑና አልቅሱ፤ ሳቃችሁን ወደ ልቅሶ፥ ደስታችሁንም ወደ ኀዘን መልሱ ፥ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ እርሱም ከፍ ከፍ ያደርጋችኋል። » እያሉ አስተምረዋል። ያዕ ፬፥፱
ኀዘን ሲባል ሁለት ዓይነት ነው። አንደኛው የማይገባ ኀዘን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የሚገባ ኀዘን ነው።
መኑ አንተ? አንተ ማነህ?
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በሃይማኖት ለወለደቻቸዉ ልጆቿ ብቻ ሳትወሰን ለኢትዮጵያዉያን ወገኖቿ ሁሉ የመጀመሪያዉን ትምህርት ቤት በመክፈት ሥነ ጽሑፍን፣ ሥነ ጥበብን፣ ሥነ ስዕልን፣ አስተዳደርን፣ በብቃትና በትጋት አስተምራለች። ከዚህም ጋር በጋራ የአገር ድንበር መጠበቅን፣ በሀዘን በደስታ ተባብሮና ተደጋግፎ መኖርን፣ ለትዉልድ ሁሉ አበርክታለች። አበዉ እንደሚሉት ታሪክ ትልቅ ትምህርት ቤት ከመሆኑም በላይ መስተዋት ነዉና ከመልካም ታሪኳ እንደተማርነዉና እንደተረዳነዉ እዉነተኛ ልጆቿን ለይታ የምታዉቅ በመሆኗ መልካም ስምን ሰጥታ ሞግስን እና ክብርን አጎናጽፋ ትልቅ ትንሽ፣ ነጭ ጥቁር፣ ሩቅ ቅርብ፣ ዘመድ ባዕድ ሳትለይ እናትነቷን አዉቀዉ፣ ጥሪዋን ሰምተዉ፣ ሥራቷን ተቀብለዉ፣ ሕጓን አክብረዉ ለሚመላለሱት ሁሉ አድልዎ በሌለበት የእናትነት ፍቅሯ የማይጠፋ የዘለዓለም ስምና ክብር ከድል አክሊል ጋር አቀዳጅታለች። አገራችን ኢትዮጵያ የአኩሪ ታሪክ ባለቤት ለመሆን ካበቃትም ምክንያት አንዱና ዋናዉ ሀገረ እግዚአብሔር መሆኗ ነዉ። ጥንትም በዘመነ ብሉይ በኋላም በዘመነ ሐዲስ ከእግዚአብሔር ያልተለየች አገር ስለሆነች ልጆቿን በፈሪሃ እግዚአብሔር፣ በሃይማኖት፤ በጥበብ፣ በእንግዳ ተቀባይነት፣ በወገን ወዳድነት አሳድጋለች።